Cifra Club

Das Tal (Ansaw)

Teddy Afro

Aún no tenemos los acordes de esta canción.

ዳስ ጣል ልቤ
ለይውስጤ ሀዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ

አለ ጊዜ
ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልኩት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ

እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት
የት ያለቅሳል ሄዶ

ዳስ ጣል
ዳስ ጣል

ዳስ ጣል ልቤ
ለይውስጤ ሀዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ

አለ ጊዜ
ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልኩት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ

እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት
የት ያለቅሳል ሄዶ

ዳስ ጣል
ዳስ ጣል

አክሱም ላሊበላን
በአንድ አለት አፅንቶ
አልራመድ አለ

ሀገር ተለያይቶ
ምሰሶው ዘመመ
ጣራውም ያፈሳል

ሀገር የሞተበት
የት ሄዶ ያለቅሳል
የት ሄዶ ያለቅሳል

ባሳደገኝ ቀዬ
ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሆኜ

እንደሌለው ሀገር
ያቆምኳትን ሰንደቅ
ተፈትኜ በእሳት

እንዴት አቀርቅሬ
ባንዲራዬን ላንሳት
ባንዲራዬን ላንሳት

አባይ ለዘዴው
በአፍ ይቀድማል
አምኖ መከዳት

እንዴት ያማል
ወርቅ ያበደረ
ደርሶት አለት

እንዴት ይችላል
ዝም ማለት

ከነገ ዛሬ
ይሻል ባልኩኝ
የራሴን ጩኸት ተነጠኩኝ

ተጣላሁና ከውንዜ አድባር
እንዴት ልታረቅ ከራሴ ጋር

አዲስ አበባ
አዶ ሸገሩ
እንኳን ሸገሩ

የሁሉ አይደል ወይ
ሞላው ሀገሩ
ሞላው ሀገሩ

በፍቅር ጠርተን
ከዳር እስከዳር
ከዳር እስከዳር

መሀል ገቡና
አቆሙን ከዳር
አቆሙን ከዳር

ባቆዩት ሀገር
ጀግኖች በአንድነት በአርበኝነት
እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጲያዊነት

ባቆዩት ሀገር
ጀግኖች በአንድነት
ጀግኖች በአንድነት

እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት
እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት
እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት

ጀግኖች ሞተውላት
በመርዝ ጋዝ ነፍረው
ተንገብግበው በእሳት

ዘመን ተገላብጦ
እንዴት አቀርቅሬ
ባንዲራዬን ላንሳት

ዘመን ተገላብጦ
እንዴት አቀርቅሬ
ባንዲራዬን ላንሳት

የኢትዮጵያ አርበኞች
የጥንት አርበኞች
እነ አናብስቱ

ሲረገጥ ባንዲራው
ገና አሁን ሞት
ካለቦታው ሲሆን

ወርቅ አይደለምና ዝምታ
ለበግም አልበጃት
አስራ ሁለት ሆና

አንድ ነብር ፈጃት

ተው ተው ተው ተው
ዳስ ጣል ልቤ ደስ ጣል (ዳስጣል)
ከዚህ በላይ ሀዘን

ከዚህ በላይ መርዶ
ከወዴት ይመጣል (ዳስጣል)
ፍቅርን ብዬ እንጂ

ተግቼ ለሰላም እኔስ መታገሴ (ዳስጣል)
መች ከሀገር ይበልጣል
እኔስ አንድ ነብሴ (ዳስጣል)

መች ከሀገር ይበልጣል
እኔስ አንድ ነብሴ (ዳስጣል)

(ወደላይ)
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን
ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን

ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን
ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን

ወይድ አታስቆጥረኝ ደም አጥንቴን
እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን

ወይድ አታስቆጥረኝ ደም አጥንቴን
እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን

ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራዬን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማዬን

ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራዬን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማዬን

ባንዲራዬን (አንሳው)
ባንዲራዬን (አንሳው)
ባንዲራዬን (አንሳው)
በል አንሳው (አንሳው)
አንሳው አንሳው (አንሳው)
በል አንሳው (አንሳው)
ባንዲራዋን (አንሳው)
አላማዋን (አንሳው)
ባንዲራዋን (አንሳው)
አ (አንሳው)
በል አንሳው (አንሳው)
ወደላይ (አንሳው)
በል አንሳው (አንሳው)
ወደላይ (አንሳው አንሳው)
ወደላይ (አንሳው አንሳው)
ወደላይ (አንሳው አንሳው)
(አንሳው አንሳው አንሳው)
(አንሳው አንሳው አንሳው)
(አንሳው አንሳው አንሳው)

Otros videos de esta canción
    0 visualizaciones

    Afinación de los acordes

    Afinador en línea

    Ops (: Contenido disponible solo en portugués.
    OK