አይከብድም ወይ በልብ ያለን ሰው መርሳት?
አይከብድም ወይ? አይከብድም ወይ?
እስኪ አንቺን ልጠይቅሽ ባንዴ ልብ ይቆርጣል ወይ?
እንዴት እንዳቃተኝ እኔን ምነው ባየሽ?
እህ
ተጓዡ ልቤ ደጋግሜ ብገስፀው ባሰበት፤ ሆድ ሊያብሰኝ ባሰበት ኤሄሄሄሄሄ
እንኳን ሊመለስ አንቺን እያለ መባዘኑን ገፋበት
ማረፊያ ሳጣ ያንን ጊዜ ዞር ብዬ ሳስበው ልንለያይ የቻልነው ኦሆሆሆሆሆ
"ከመለያየት ሌላ አማራጭ አልነበረም ወይ?" አላለው
አማራጭ ነበር ሳስበው አኔ
እምቢ አልሽ እንጂ እምቢ ስል አኔ
እንዲህ ላትረሺኝ ኡ ላይረሳሽ ጎኔ ላይረሳሽ ጎኔ
እርሳት ይለኛል፤ እርግፍ አድርጌ አንቺን ለመርሳት እኔ አልቻልኩኝም
እርሳት ይለኛል፤ ወሬ አይደበቅ አንቺም ጨክነሽ አልረሳሽኝም፣ ፍቅሬ አልተውሽኝም
እርሳት ይለኛል፤ ታዲያ ካቃተው ልባችን መቁረጥ ብንወስንም
እርሳት ይለኛል፤ ባለማስተዋል የሆነ ስህተት ሳንሰራ አንቀርም፣ ያኔ አላየንም
ኤሄሄሄሄሄሄሄ ኤሄሄሄሄ
አሀሀሀሀ ኡ ኤሄሄሄሄ
አይከብድም ወይ በልብ ያለን ሰው መርሳት?
አይከብድም ወይ? አይከብድም ወይ?
እስኪ አንቺን ልጠይቅሽ ባንዴ ልብ ይቆርጣል ወይ?
እንዴት እንዳቃተኝ እኔን ምነው ባየሽ?
እህ
ነጎደ ጊዜው፣ እያየነው ገሰገሰ እንደቀልድ እድሜም ሄደ እንደቀልድ ኤሄሄሄሄሄሄ
ስንት ትዝታ ማየት ስንችል ስንት ፍቅር መዋደድ
አልሆነኝ አኔ፣ አንቺም ይኸው ካልተለተለየሽ ከጭንቀት ወይ ካልሸሸሽ ከጭንቀት ኦሆሆሆሆሆሆ
ይቅር ለእግዚአብሔር ብንባባል አስኪ ምን ነበረበት
ተይ አልረፈደም አሁንም የኔ
በእግዜር መንገድ እንሂድ በወኔ
በይ አንቺም ተይው ኡ በይ ተዉኩት አኔ በይ ተውኩት አኔ
እርሳት ይለኛል፤ እኔ አምኛለው፣ ያኔ ማጥፋቴ አሁን ገብቶኛል
እርሳት ይለኛል፤ ከበቂ በላይ አንቺን ማጣቴ አስተምሮኛል ብዙ አሳይቶኛል
እርሳት ይለኛል፤ መቼም ከስህተት የፀዳ የለም፣ ስህተት ሰርተናል
እርሳት ይለኛል፤ ታዲያ ካለፈው ፍቅሬ ብንማር ቆይ ምን ይለናል፣ ፍቅር ይሻለናል
ኤሄሄሄሄሄሄሄ ኤሄሄሄሄ
አሀሀሀሀ ኡ ኤሄሄሄሄ